Sunday, September 18, 2016

The Long History of Rundassa


By: TesfayeGebreab
Translated by: Silvana Nagga

He left the place he was born and raised at, and crossed the border for hunting in a place known for its dense forest. He was riding his horse in the middle of the forest, wandering and admiring the scenery.  He was awakened from his deep fascination by the fact that he drifted off his trailer and he is lost in the middle of nowhere. He was worried as he could not maneuver around the dense forest and he does not know which way to go.  He then suddenly sees a farmer walking around his path; and he felt so relieved.  And the famer felt surprised. 

Friday, February 19, 2016

ከመባለግ መሳሳት ይሻላል


ሃይሌ ገብረስላሴ ላይ ሰሞኑን በወረደበት ድብደባ በጣም ተገርሜያለሁ። ሃይሌ የፖለቲካ ሰው አይደለም። የተናገረው የአፍ ወለምታም ሊሆን ይችላል። በፖለቲካው በኩል ተፅእኖ የማድረግ ችሎታውም ያን ያህል አይደለም። ምንድነው ይሄ ሁሉ ጩኸት? ደግሞስ ምን ስህተት ተናገረ?

Abay Tsehaye’s War

By: Tesfaye Gebreab
Translated by: Silvia Nagaa

Abbay Tsehaye has started to be the center of discussion around the issue of the recent Oromia uprising. We’ve been reading also some of his incendiary talks. It sounds like he is exerting a new behavior. Abbay was only known for his passive aggressiveness. Bu he seem to lose control when discussing issues about the Oromia uprising. He and his friends are trying their best to overcome the challenge they are facing; who knows if they succeed?

Wednesday, October 17, 2012

Tuesday, September 4, 2012

የሞትንም እኛ! የነገስንም እኛ!

ኢህአዴግ ሞተ! ኢህአዴግ ነገሰ! ለሞትነው እዘኑ! ለነገስነው ተደሰቱ! (ዘሞትነ ንህነ፣ ወዘነገስነ ንህነ፣ ሕዘኑ ወለዘሞትነ፣ ተፈስሁ ወለነገስነ) የሚል በረከተ - አዋጅ ከእንጦጦ ተሰማ። በአዋጁ መሰረት ሳይሆን፣ በባህላችን መሰረት ለቀድሞ አለቃዬ እስከ ሳልስት ሃዘን ተቀምጫለሁ። መለስ በስልጣን ዘመኑ ለሰራው ሃጢአት አምላክ ነፍሱን ይቅር ይላት ዘንድም ተመኝቻለሁ። እንግዲህ ከሳልስት በሁዋላ ህይወት ትቀጥላለች.....

Friday, August 31, 2012

ጎሹም ሄደላችሁ… (April 17th, 2012 )

የኮሎኔል መንግስቱን መፅሃፍ ሳነብ ከገረሙኝ ነገሮች አንዱ የኮሎኔል ጎሹ ወልዴን ስም አለመጥቀሱ ነበር። ቢያንስ፣ “የታጠቅ ጦር ሰፈር አመሰራረት” በሚለው ምእራፍ ስር እንኳ ስሙን ሊያነሳው በተገባ።

Wednesday, August 29, 2012

የግንቦት ማስታወሻ


እነሆ! ዛሬ ቅዳሜ ነው።
እለቱም ግንቦት 9፣ 2009።
 
ትናንት ደግሞ ግንቦት 8 ነበር። በአበሻ የዘመን አቆጣጠር ልክ የዛሬ ሃያ አመት ግድም “ጥቂት ጄኔራሎች” ኰሎኔል መንግስቱ ላይ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አድርገው ነበር። ሳይሳካላቸው በመክሸፉ ዛሬ በህይወት የሉም። ማንኛውም አጥንት – አስከሬን ሆነዋል። አምላክ የጄኔራሎቹን ነፍስ ይማር። እኒያ ሰዎች ከነሙሉ ችግራቸው ከኰሎኔል መንግስቱ የተሻሉ ዜጎች ነበሩ ብዬ አምናለሁ።

የበረከት መፅሃፍ

- 1 -
የበረከትን መፅሃፍ አነበብኩት…
በእውነቱ ህትመቱ ቆንጆ ነበር። ሽፋኑ እንደ ሃብታም ጉንጭ ይለሰልሳል። ከቻርልስ ዲክንስ ታዋቂ መፅሃፍ የተኮረጀ ቢሆንም ርእሱም ቢሆን አሪፍ ነው - የሁለት ምርጫዎች ወግ። የበረከትን መፅሃፍ ያሳተመው መሃመድ አላሙዲ የተባለው ነጋዴ መሆኑን ፍትህ ጋዜጣ ላይ አንብቤ ነበር። መፅሃፉ 314 ገፆች እና 10 ምእራፎች ይዞአል። ዋጋው 90 ብር ነው።


'የመለስ “ጠንካራ” ጐን! (April 27th, 2011 at )

ከጥቂት ቀናት በፊት ‘ብዙ ወንድምአገኝ’ ከካናዳ ስልክ ደውላ እንዲህ ስትል ጠየቀችኝ፣
“ምነው ጠፋህ ታዲያ?”
መልስ ከመስጠቴ በፊት በግሳፄ እንዲህ ቀጠለች፣
“በአመት አንድ መፅሃፍ መፃፍ በቂ ይመስልሃል? ከሃገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ስለ ቀድሞ አለቆችህ አንድ ነገር ማለት አለብህ።”

የመለስ አልጋ ወራሾች (July, 2012)

መለስ ታመመ” የሚለውን ወሬ ተከትሎ፣ ኮማ ውስጥ መግባቱና መሞቱ እየተነገረ ሰንብቶአል። የወያኔ መንግስት ግን ወሬውን አፍኖ ለመቆየት ተጨናነቀ። መለስ ጀርመን ሃገር ላይ ቀዶ ጥገና ህክምና ማድረጉ በአንድ ወገን ሲገለፅ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ቤልጅየም 10 ቀናት አልጋ ይዞ መሰንበቱ ተሰምቶአል።

የመለስ ቀልዶች (sep, 30 2010)

ወያኔ ጉባኤውን አዳማ ላይ አካሄደ።

እናም ጉባኤው በአትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ ንግግር ተቋጨ። መለስ ዜናዊም በሃይሌ ንግግር ሲስቅ በቴሌቪዥን ተመለከትነው። መለስ ዜናዊ፣ “በአምስት አመታት አጠናቅቀዋለሁ” ያለውን ትንግርታዊ፣ አስማታዊና ሰማያዊ የልማት እቅድ ዶክተር ሃይሌ ከመለስ ብሶ፣ “በሁለት አመታት እንጨርሰዋለን” ሲል ቃል ገባ። አያይዞም አትሌት ሃይሌ፣ “ስለ ሰከንድ ማሰብ አለብን” ሲል ተናገረ።
ሃይሌ ሃብቱንም ሆነ ክብሩን ያገኘው ባቋራጭ ሳይሆን፣ ላቡን ጠብ! አድርጎ በመሆኑ አከብረዋለሁ። የሃይሌ ክብር የግሉ ሳይሆን የሃገሪቱ ጭምር በመሆኑ ደግሞ ለሃይሌ ያለኝ አክብሮት ድርብ ነው።

መለስ ዜናዊ ከሞት እንዴት እንዳመለጠ (March 5 2012)

ትረካውን ጥቂት አሰማምሬው ይሆናል እንጂ ይህ የምገልፅላችሁ ታሪክ በትክክል የተፈፀመ ነው። ታሪኩን ካጫወተኝ ሰው ጋር ስናወራ፣
“ልፃፈው?” ስል ጠየቅሁት።
ሳቀ! በጣም ሳቀ! እና ፈቀደልኝ።
“ፃፈው! ድክመታችንን ያሳያል …” አለ።

መለስ ዜናዊ በማን ይተካል? (April 1 2012)

ወቅታዊውን የኢትዮጵያ የፖለቲካ የሃይል አሰላለፍ በመገምገም፣ “መለስ ዜናዊ! – በማን ይተካል?” ለሚለው ጥያቄ ምላሽ መስጠት በርግጥ ቀላል አይደለም። በቅድሚያ ግን “በርግጥ መለስ ዜናዊ ስልጣኑን ይለቃል?” ብሎ መጠየቅ ይገባል። መለስ ዜናዊ፣ “ከሁዋላ ሆኜ ማገዜ ባይቀርም፣ እለቃለሁ” ብሎ ደጋግሞ ነግሮናል። ተቃዋሚዎች በበኩላቸው፣ “መለስ እለቃለሁ ቢልም ባይልም አፍንጫውን ተይዞ ይለቃል” ሲሉ ቁጣ ባዘለ ድምፅ እየገለፁ ነው። የሆነው ሆኖ በራሱ ፍላጎትም ሆነ ተገዶ መለስ ስልጣኑን መልቀቁ የማይቀር ከሆነ ቀጣዩ የኢትዮጵያ መሪ ማን ይሆናል? በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ ተንትኖ የፃፈ አላጋጠመኝም…