ቅንጭብጭብ


‹‹መለስ እራሱን ብቻ ሳይሆን ሀወሓትንም ጭምር ገድሎ ነው የሞተው:: በትጥቅ ትግሉ ወቅት የጎላ ድርሻ የነበራቸውና ችግርና መከራን ተጋፍጠው ህወሓት ውስጥ በጽናት የዘለቁ አመራሮች ወደ ጎን ተገፍተው፤ ዛሬ ድርጅቱ የእነ አዜብ መፈንጫ ሆኗል››
ስብሐት ነጋ (አውራምባ ታይምስ)
 
“….ዛሬ እድሜያቸው 50 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎች ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር ያላትን ክብርና ሞገስ ማወቅ ቀርቶ መገመትም አይችሉም። ኢትዮጵያ የለማኞችና የስደተኞች አገር ከሆነች በኋላ፤ የሚያኮሩና ሃውልት ልንሰራላቸው የሚገባንን አርበኞች ገድለን ባንዶችን ወንበር ላይ ካወጣን በኋላ፤ ኢትዮጵያ በሶማሊያ በአስር ቀኖች እስከ ጅጅጋ በሶማሊያ ከተወረረች በኋላ፤ የኢትዮጵያ ጦር በሻቢያና በወያኔ ጀሌዎች ከተሸነፈ በኋላ፤ ኤርትራ ተገንጥላ ኢትዮጵያ ወደብ አልባ ከሆነች በኋላ፤ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ጥራት እንዘጭ ብሎ ከወረደ በኋላ፤ ኢትዮጵያ ከኳስ ጨዋታው ዓለም ከተሰናበተች በኋላ፤ በጫጨ የወያኔ የታሪክ ግንዛቤ የብዙ ሺህ ዓመታት የታሪክ ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ በመቶ አመት ከተወሰነች በኋላ፤ አክሱም ፅዮን፤ ደብረ ዳሞ፤ ደብረ ቢዘን በወያኔ ደፋር መሀይማን ከኢትዮጵያ ከተለዩ በኋላ፤ የአክሱም መንግስት ከአድዋ አያልፍም ከተባለ በኋላ፤ ኢትዮጵያዊነት በጎሰኝነት ተቆርጦ ድንክዬ ከሆነ በኋላ እንደዚህ ኢትዮጵያ ወርዳ ወርዳ እንዘጭ ካለች በኋላ የተፈጠሩ ኢትዮጵያዊያን በርትተው የአገራቸውን ታሪክ ካልተማሩ ለልጆቻቸው የሚያስተላልፉት ውርደት ብቻ ይሆናል…”
የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም  “አደጋ ያንዣበበበት የአፍሪካቀንድ