የኢትዮጵያ ደራስያን በስማቸው ቴምብር ታተመ።
|
ካንድ ልብስ ሰፊ - መደብር ገባና፣
አንድ እውነተኛ ጅል - ከመድረሱ ገና፣
በጣም ደስ ብሎት - ከልቡ እየሳቀ፣
“ልብስ ሰፊው የት ነው?” - አለና ጠየቀ።
ወዲያው ቀረበና - ወደ ልብስ ሰፊ፣
የኮት ቁልፎች አሉኝ - ያማሩ ሰፋፊ፣
አስቤያለሁና ሳይጠብም ሳያጥር፣
ኮት እንድትሰፋልኝ - ስፌቱ የሚያምር፣
ዋጋው እንዳይጎዳኝ - ብረዳህ ይበጃል፣
ቁልፍ እኔ ስሰጥህ - ሌላው ምን ይፈጃል?
(ግጥም - ከበደ ሚካኤል)