ሹክሹክታ

አባዱላ እየተለመነ ነው
          አባዱላ ገመዳ “የኦሮሚያን የፕሬዚዳንትነት ስልጣን አልረከብም” በማለቱ እየተለመነ መሆኑ ተሰምቶአል። በርግጥም አባዱላ ከኦሮሚያ ሲባረር በግምገማ ከፍተኛ ውርደት ደርሶበታል። በሙስና ተወንጅሎ በሂስ በረዶ ተደብድቦአል። ግብረአበሮቹ ተመንጥረዋል። “ሊታሰር ይገባል” ሲሉ ጭምር የዛቱበት ነበሩ። ከዚህ ሁሉ በሁዋላ፣ ለህወሃት ታማኝ በመሆኑና ከአዜብ መስፍን ጋር በነበረው የቀረበ ግንኙነት ምክንያት የፓርላማው መዶሾ እንዲሰጠው ተደርጎ ነበር። ኢህአዴግ አሁን ውጥረት ውስጥ ሲገባ ወደ አባዱላ ለመመለስ ተገዶአል። አባዱላ ያንገራገረው፣ ጠላቶቼ የሚላቸውን ለመመንጠር የሚያስችለውን ሙሉ ስልጣን ለማግኘት ፈልጎ ነው ተብሎ እየታማ ሲሆን፣ ወደ ኦሮሚያ ፕሬዚዳንትነት ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል።