የኢትዮጵያ ደራስያን በስማቸው ቴምብር ታተመ



የኢትዮጵያ ደራስያን በስማቸው ቴምብር ታተመ።
ካንድ ልብስ ሰፊ - መደብር ገባና፣
አንድ እውነተኛ ጅል - ከመድረሱ ገና፣
በጣም ደስ ብሎት - ከልቡ እየሳቀ፣
“ልብስ ሰፊው የት ነው?” - አለና ጠየቀ።
ወዲያው ቀረበና - ወደ ልብስ ሰፊ፣
የኮት ቁልፎች አሉኝ - ያማሩ ሰፋፊ፣
አስቤያለሁና ሳይጠብም ሳያጥር፣
ኮት እንድትሰፋልኝ - ስፌቱ የሚያምር፣
ዋጋው እንዳይጎዳኝ - ብረዳህ ይበጃል፣
ቁልፍ እኔ ስሰጥህ - ሌላው ምን ይፈጃል?
(ግጥም - ከበደ ሚካኤል)


"ቁጥር 1" ቴምብር ሀዲስ አለማየሁ፣ ጸጋዬ ገ/መድህን፣ ስንዱ ገብሬ እና ከበደ ሚካኤልን ያካተተ ሲሆን - በ"ቁጥር 2" ደግሞ ተመስገን ገብሬ፣ ብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደስላሴ፣ ዮፍታሄ ንጉሴ እና አፈወቅ ገብረየሱስ ይገኙበታል፡፡